ኢትዮጵያ ለሰው ልጅ መገኛነት የመጀመሪያ አሻራ ያላት ሃገር ናት:: በሁለቱ ሃገሮች መካከል ያለው ግንኙነት በታሪክ ሂደትና በትላልቅ የጋራ ፕሮጀክቶች ላይ የተመሰረተ ነው።. እ.ኤ.አ. በ 2019 መሰረታዊ የሆኑ የባህልና የቅርስ ጥበቃን ከሳይንሳዊ ፕሮግራም ጋራ አያይዘን ለመስራት ወስነን ተነስተናል። በላሊበላም የሰራነው በዓለም ላይ ልዩ የሆነ የቅርስ ጥበቃ ፕሮጀክት በሚቀጥሉት ወራት ውስጥ ፍጻሜውን የሚያገኝ ይሆናል። በአንድ ወቅትም የብሔራዊ ቤተ መንግሥት እድሳት ፕሮጀክትንም ሰርተን ዛሬ የሚያኮራ እውነታ ሆኖ እየታየ ነው። ወደፊትም የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ማሻሻያ ማዘመንን ለመደገፍ እና በትግራይ የሰላምና የመረጋጋት መሰረት የሆነውን የፕሪቶሪያ ስምምነትን ተግባራዊ ለማድረግ ትብብር እናደርጋለን። የተከበሩ ጠቅላይ ሚንስትር @AbiyAhmedAli የወደፊቷ የኢትዬጵያ ተስፋ የብልጽግናና የሰላም እንደሚሆን ፈረንሳይ እምነቷ ነው።